Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው እለት መጀመሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡

52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሲጀመር በሴቶች ርዝመት ዝላይ፣ በወንዶች ከፍታ ዝላይ የፍጻሜ፣ እንዲሁም በ800 ሜትር ወንዶችና ሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ተካሄደዋል።

የውድድሩ ዓላማ በፈረንጆቹ ከታህሳስ 19 እስከ 27 ቀን 2023 ድረስ በሃንጋሪ – ቡዳፔስት ለሚካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌቶች አቋማቸውን እንዲለኩ እድል ለመፍጠር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በክለቦችና በማሠልጠኛ ማዕከላት ለሚገኙ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፣ተተኪ አትሌቶችንም ለማፍራት ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኝ ሻምፒዮና ሲሆን፥ ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከግንቦት 8 እስከ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

ቀደም ባሉት ዓመታት ኢትዮጵያ በአህጉራዊ፣ በዓለም አቀፍና በኦሊምፒክ የውድድር መድረኮች በመሳተፍ ድል የተቀዳጁ፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረጉ ጀግና አትሌቶች ተሳትፈው ያለፉበትና የሚሣተፉበት የውድድር መድረክ ነው መባሉን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.