Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ ከኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ዲሚትሪ ሉካሼንኮን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በዚህ ወቅት የክብር ቆንስሉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን በምስራቅ አውሮፓ በመወከል ላሳዩት ቁርጠኝነት አቶ ደመቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አያይዘውም “እርስዎ በቤላሩስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነዎት” ሲሉ ገልጸውላቸዋል።

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያና ቤላሩስ በተለይም በኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ ግብርና ሜካናይዜሽን እና በማዕድን ዘርፍ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እንደሚያደርጉ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ዲሚትሪ ሉካሼንኮ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

አያይዘውም በኢትዮጵያ የሚታየውን እድገትና አወንታዊ ለውጥ አድንቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.