Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ስራን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ስራን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ላይ የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ያለበት ደረጃ በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ የፕሮጀክት ተጠሪ መሀንዲስ መስፍን ኃይሉ(ኢ/ር) ከይዞታ ወሰን ማስከበርና በአካባቢው ከዝናብ መብዛት ጋር ተያይዞ ግንባታው መዘግየት ያጋጠመው መሆኑን በገለጻቸው አብራርተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የአውሮፕላን ማረፊያው መገንባት በአካባቢው የሚመረት ቅመማ ቅመምን ጨምሮ የግብርና ምርት ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ አስተዋጽኦው የላቀ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል።

በግንባታው ሂደት በተለይም ከይዞታ ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ለተስተዋሉ ክፍተቶች መፍትሄ ጥረት እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር ለግንባታው ስኬት እያደረገ ያለውን እገዛ በማድነቅ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት መሆኑ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.