Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሩሲያ ላዕላይ ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሩሲያ ላዕላይ ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

የመግባቢያ ሰነዱን የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና የሩሲያ ፌዴሬሽን የፌዴራላዊ ሸንጎ አፈጉባኤ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ተፈራርመዋል።

በሞስኮ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት አፈጉባኤ አገኘሁ፥ በቆይታቸው በሁለቱ አገራት እና በምክር ቤቶቹ መካከል ያለው ግንኙነት በሚጠናከርባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

ከአፈጉባኤ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይም፥ ሩሲያ ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ስትደግፍ መቆየቷን አንስተዋል።

አሁን ላይም ኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን ጨምሮ ሩሲያ ኢትዮጵያን መደገፏን መቀጠሏን ጠቁመዋል።

አፈጉባኤ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ በበኩላቸው፥ ሁለቱ አገራት የዛሬ 125 ዓመት ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ከመሠረቱ ጀምሮ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሩሲያ ቁልፍ አጋር ሆና መኖሯን ተናግረዋል።

ሁለቱ አፈጉባኤዎች ሀገራቱ በንግድ፣ ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.