Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል፣ የሐረሪና የድሬዳዋ የሥራ ኃላፊዎች የግብርና ሣይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ የግብርና ሣይንስ አውደ ርዕይ ጎበኙ።

በጉብኝቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮች፣ የሐረሪ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የግብርና ቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ለጎብኚዎቹ በግብርና ዘርፍ እና በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገቡ ውጤቶች ላይ በባለሙያዎች ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡

“ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው አውደ ርዕዩ የተሻሉ የግብርና ምርምር ፈጠራ ስራዎች፣ የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችም ቀርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.