Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላት ያሉት የአማካሪ ኮሚቴ አቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላትን ያቀፈ የአማካሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከኮሚቴው አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ አዘጋጅቷል።

በኮሚቴው እንዲካተቱ የተጋበዙ ግለሰቦች በተለያየ መልኩ ለኮሚሽኑ ስራዎች ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን በተለያየ ልምድ እና ሙያ ውስጥ መኖራቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

አባላቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እንዲሁም በምክክር ሂደት ላይ ስራዎችን ያከናወኑ ግለሰቦች እና የተቋማት ተወካዮች መሆናቸውም ተገልጿል።

ኮሚሽኑ ይህንን ኮሚቴ ሲያቋቋም በተቋቋመበት አዋጅ 1265/2014 ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን መሰረት በማድረግ መሆኑን ጠቅሶ፥ ለኮሚቴው ስራዎችን የሚያከናውንበትን የውስጥ መመሪያ ማዘጋጀቱንም ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በኮሚሽኑ የተከናወኑ ዋና ተግባራትን እና በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱ ስራዎችን በተመለከተ ለኮሚቴው አባላት ገለፃ አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.