Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ሙቀት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊያልፍ እንደሚችል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ቢያንስ አንዱ አመት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሞቃታማ እንደሚሆን የዓለም የአየር ትንበያ ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

የሙቀት አማቂ ጋዞች እና ኤልኒኖ በመጣመር የሙቀት መጠኑን እየጨመሩ በመሆኑ÷ ቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሞቃታማ ወቅት እንደሚሆኑም የተባበሩት መንግስታት አስጠንቅቋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ሙቀት በፈረንጆቹ እስከ 2027 ድረስ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ  ወይም 2 ነጥብ 7 ዲግሪ ፋራናይት በላይ ሙቀት የመጨመር  እድል እንዳለው የዓለም የአየር ትንበያ  ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም የአየር ትንበያ  ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፔትሪ ታላስ÷ ተፈጥሯዊው ክስተት በሰዎች ምክንያት ከሚፈጠረው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በመጣመር የዓለምን የሙቀት መጠን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል።

ይህ ሁኔታም በጤና፣ በምግብ ዋስትና፣ በውሃ አያያዝ እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ስለሚኖረው ዝግጁ መሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የማሌዢያ የአየር ንብረት ጉዳይ ምክር ቤት ባለሙያ ጀሚላህ ማህሙድ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት÷ “አደጋው ላደጉትም ሆነ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ለሚኖሩ  ሰዎች ሁሉ እደሚሆን አብራርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.