Fana: At a Speed of Life!

ለሱዳን ቀውስ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት 209 ሚሊየን ዶላር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በሱዳን በተፈጠረው ቀውስና ሁከት ለተጎዱ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 209 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል ብሏል።

የሱዳን ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱ በጎረቤት ሀገራትም ላይ ተጥዕኖ እያሳደረ መምጣቱንም ነው የገለጸው፡፡

ከ209 ሚሊየን ዶላሩ ውስጥ 105 ሚሊየን ዶላሩ በሱዳን ላለው ቀውስ እንደሚያስፈልግም ድርጅቱ ገልጿል።

104 ሚለየን ዶላሩ ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብፅ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ቻድ እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከቀውሱ ጋር በተያያዘ ለሚደረገው ድጋፍ ያስፈልገኛልም ነው ያለው።

በተጨማሪም በሱዳን እና በአጎራባች ሀገራት ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ 37 ሚሊየን ዶላር እንደሚያሰፈልግም አስታውቋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ “አሁን በሱዳን ያለው ሁኔታ ሀገሪቱ እስካሁን ካየችው እጅግ የከፋው ነው” ብለዋል።

በሱዳን በተፈጠረው ቀውስ ሚሊየኖች መሰረታዊ የውሃ፣ የምግብ እና መጠለያ ድጋፍ እንደሚሹም ነው የገለጹት፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን እርምጃ ካልወሰድን የሱዳን ህዝብ ከዚህ የከፋ ችግር ይገጥመዋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ድርጅቱ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከሱዳን ቀውስ ጋር ተያይዞ እስካሁን ወደ 25 ነጥብ 7 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በሱዳን እና በድንበር አካባቢ ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

ወደ 259 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከሱዳን ሸሽተው ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውም ነው የተገጸው፡፡

አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ መሻሻል የማያሳይ ከሆነ የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚያሻቅብና ጎረቤት ሀገራትም የቀውሱ ገፈት ቀማሽ እንደሚሆኑ ድርጅቱ አስጠንቅቋል።

#Ethiopia #Sudan #SudanCrisis

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.