Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 7 አባል ሀገራት በሩሲያ ላይ ማዕቀባቸውን ይበልጥ ለማጥበቅ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትወስደውን እርምጃ እንድታቆም ለማስገደድ የቡድን 7 አባል ሀገራት ማዕቀባቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እየመከሩ ነው፡፡

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ጉባዔ ከዕለተ አርብ ጀምሮ በጃፓን ሄሮሺማ እየተካሄደ ነው፡፡

ምንም እንኳን ሀገራቱ በሩሲያ ላይ እስካሁን የጣሉት ማዕቀብ ጠንካራ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ቢሆንም የቡድኑን አባል ሀገራት በሚፈልጉት ልክ እንዳላረካ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በመሆኑም ሀገራቱ ቀድሞ በነዳጅ እና ኃይል አቅርቦት ሞስኮ ላይ ከጣሉት ማዕቀብ በተጨማሪ አዲስ እና ኃይል ተኮር ባልሆኑ የንግድ እንቅስቃሴዎቿ ላይም ጭምር ማዕቀብ የመጣል ሃሳብ እንዳላቸው ነው የተሰማው።

አሜሪካ ፣ ካናዳ ፣ ጃፓን ፣ እንግሊዝ ፣ ፈረንሣይ ፣ ጀርመን እና ጣሊያን፥ ቡድኑ ሩሲያ ላይ የሚጥለው ተጨማሪ ማዕቀብ ፍሬ እንዲያፈራ የምጣኔ ሐብት ማዕቀቡን በማጥበቅ ረገድ ለመተባበር ባለፈው ቅዳሜ በነበራቸው ውሎ የየሀገራቱ የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የማዕከላዊ ባንክ ገዢዎች ቃል መግባታቸውም ተመልክቷል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል፥ አባል ሀገራቱ ከሩሲያ ሲያስገቡ በነበረው የነዳጅ አቅርቦት ፋንታ የሕንድን የኃይል አማራጮች እና ነዳጅ እንዲጠቀሙ ምክረ-ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

በአንጻሩ ሩሲያ ተደጋጋሚ ማዕቀብ ቢጣልባትም ወደ ቻይና ፣ ሕንድ እና ቱርክ የምትልከውን የድንጋይ ከሰል እና የነዳጅ የወጪ ንግድ ግብይት ከፍ ማድረጓ ነው የሚነገረው።

በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ በሩሲያ ማዕቀብ ጉዳዮች ላይ የሚሰራው ቡድን አባል የሆኑት ራቼል ሉካዝ ደግሞ የሩሲያ የቴክኖሎጂ እና የንግድ ዘርፎች የአባል ሀገራቱ የማዕቀብ ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.