Fana: At a Speed of Life!

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ በቻይና ቤጂንግ የተለያዩ ኩባንያዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑካን ቡድን በቻይና ቤጂንግ በሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች ጉብኝት አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረት ልዑኩ ’ቤጂንግ ኢኮኖሚክ ቴክኖሎጂ ልማት’ የተሰኘ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

የኢኮኖሚ ዞኑ ከ40 በላይ ሀገራት የተውጣጡ እና ከ100 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ያደረጉ 26 ሺህ አምራች ኩባንያዎችን የያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡

በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ ለበርካታ በሽታዎች የተለያዩ መድሃኒቶችን በማምረት የሚታወቀውን ’ዩ ኬር’ የተሰኘውን ፋርማሲዩቲካል ኩባንያ መጎብኘቱ ተገልጿል፡፡

በመቀጠልም ልዑኩ ‘ኤስ ኤም ሲ አውቶሜሽን’ የተባለውን እና ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የአውቶማቲክ መቆጣጠሪያዎችን የሚያመርተውን ኩባንያ ጎመጎብኘቱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ልዑካኑ ‘ፖኒ ኤ አይ’ የተሰኘውን ያለ ሰው ዕርዳታ በራሳቸው መንቀሳቀስ የሚችሉ መኪኖችን የሚያመርተውን አምራች ኩባንያም ጎብኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.