Fana: At a Speed of Life!

የኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን የልማት አጀንዳ እንጂ የትኛውንም አካል ለመጉዳት ያለመ አይደለም – በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያውያን የልማት አጀንዳ እንጂ የትኛውንም አካል ለመጉዳት ያለመ አለመሆኑን በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር እፀገነት ይመኑ ገለጹ፡፡

አምባሳደር እፀገነት ይመኑ ከናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ዋና ፀሐፊ ሲይልቪስተር አንቶኒ ጋር በካምፓላ ተገናኝተው መወያታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸው ወቅት አምባሳደሯ÷ የግድቡን የሦስትዮሽ ድርድር ጉዳይ አንስተው ከአፍሪካ ማዕቀፍ ውጪ መፍትሄ ለማምጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ እስካሁን ባከናወናቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች እና ቀጣይ መሠራት ባለባቸው የትብብር መስኮች ላይም ሐሳብ ተለዋውጠዋል።

አምባሳደር እፀገነት ÷ ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ውሃውን በፍትሃዊነት እና በተገቢ መንገድ እንዲጠቀሙ በማድረግ ረገድ በሀገራቱ መካከል ትብብር እንዲጎለብት የተጫወተውን በጎ ሚና ኢትዮጵያ እንደምታደንቅም ገልጸዋል፡፡

ይህ አቋም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠይቀዋል።

የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ሲይልቪስተር አንቶኒ በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ ተቋሙ እንዲጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጡ ካሉ ሀገራት ቀዳሚዋ መሆኗን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ኢኒሼቲቩ የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት በሚያከናውናቸው እንቅስቃሴዎች የኢትዮጵያ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.