Fana: At a Speed of Life!

60ኛ ዓመት የአፍሪካ ኅብረት ምሥረታ በዓል ከግንቦት 17 ቀን ጀምሮ ይከበራል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አንድነት/ኅብረት 60ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ከግንቦት 17 ቀን ጀምሮ እንደሚከበር ተገለጸ፡፡

በዓሉ የአኅጉሩን አንድነት በሚያጠናክሩ መርሐ- ግብሮች እና ዝግጅቶች ላይ እንደሚያተኩር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ለመገናኛ ብዙኃን ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኅብረቱ አባል ሀገራትም በየሀገራቸው የኅብረቱን ምሥረታ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብሩም በመግለጫቸውም ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ አንድነት / ኅብረት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከግንቦት 18ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ እንደሆነ ታውቋል።

በበዓሉ የፓን-አፍሪከኒዝም ለማስረፅ የተደረጉ ጥረቶች እና የቀኝ አገዛዝ ቀንበርን ለመስበር የተደረጉ ትግሎች ይዘከራሉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በ2063 የአፍሪካ ኅብረት ለማሳካት የያዘቻቸው ግቦች እንደሚወሱበት ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዓሉን የምታከብረው የኅብረቱን ዓላማ ለማሳካት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን በማጉላት እና የአዲስ አበባን የዲኘሎማሲ ማዕከልነት ለማፅናት በሚያስችል ሁኔታ እንደሆነ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.