Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂዎች መውጫ ፈተና ከፊታችን ሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ ይሰጣል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
 
የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።
 
በ2014 ዓ.ም የሕግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።
 
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.