Fana: At a Speed of Life!

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ከኮሎምቢያ ባህል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ ከኮሎምቢያ ባህል ሚኒስትር ጆርጅ ዞሮን ጋር በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ ÷ ኢትዮጵያ ያላትን ባህላዊ እሴቶችና የጥበብ ዘርፍን በማልማት ለማህበራዊ ትስስር እና ለኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ከኮሎምቢያ ጋር በባህልና በጥበብ ልማት እና እድገት ዙሪያ አብሮ ለመስራት እንዲሁም ልምድ ለመለዋወጥ ያላቸውን ዝግጁነትና ፍላጎትም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ሚኒስትር ጆርጅ ዞሮን በበኩላቸው እንዳሉት ÷ ኮሎምቢያ እና ኢትዮጵያ የቆየ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በባህልና በጥበብ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላቸው።

ኮሎምቢያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ሀገር እና ከ65 በላይ ቋንቋ የሚነገርባት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

በዚህም ባህላዊ እሴቶች ለምተውና ተጠብቀው ለትውልድ ለማስተላለፍ ከኢትዮጵያ ልምድና ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉም ነው የተናገሩት፡፡

አቶ ቀጄላ ፥ ኮሎምቢያ በባህልና በጥበብ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ያሳየችውን ፍላጎት ማድነቃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.