Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የፓሎች – ማቲያንግ – ማይውት – ፓጋክ መንገድን ለመገንባት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የፓሎች – ማቲያንግ – ማይውት – ፓጋክ መንገድን ለመገንባት በጁባ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

መንገዱ ምዕራብ ኢትዮጵያን ከሰሜን ምስራቅ ደቡብ ሱዳን ጋር የሚያገናኝ የፍጥነት መንገድ መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

በፊርማ ስነስርዓቱ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማርዲያት የተገኙ ሲሆን÷ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና የደቡብ ሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ዴር ቶንግ ንጎር (ዶ/ር) ተፈራርመዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ÷ “ተስፋችን እርስ በእርስ ለመረዳዳት በጋራ መንቀሳቀስ ነው፤ ሕዝባችን ማየት የሚፈልገው ይህንን ነው፤ ይህ ሕዝባችንን የሚያስተሳስርና ፍላጎቶቹን የሚያሟላ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል”።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንደተናገሩት÷ የዚህ መንገድ መገንባት የሀገራቱን የንግድ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ ሰው ሰራሽ የድንበር መለያየትን በማስቀረት የእህትማማች ሀገር ህዝቦችን ይበልጥ ያቀራርባል።

በፊርማ ስነ ስርአቱ ወቅት ሀገራቱ ቀጠናዊ የኢኮኖ ውህደትን የሚያሳልጡ የኤሌክትሪክና የነዳጅ ማስተላለፊያን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን ለማጠናከር ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.