Fana: At a Speed of Life!

የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 ( ኤፍ ቢ ሲ) የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

የፌዴራል እና የክልል የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ባለድርሻ አካላት የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው፣ የሰነድ ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዳጋቶ ኩምቤ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ደጋቶ ኩምቤ፥ የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥን ተዓማኒ፣ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ለማድረግ በቅንጅት እተሠራ  መሆኑን ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ኦንላይን ለማድረግም እቅድ ተይዞ ስራ መጀመሩን ጠቅሰው፥ አሁን ላይ 80 በመቶ የሚሆነውን አገልግሎት ከሰው ንክኪ ነጻ በማድረግ ብልሹ አሰራርን መቆጣጠር መቻሉንም ነው የተናገሩት።

የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው፥ የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ለፍትህ ዘርፉ ውጤታማነት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

ዜጎች በመተማመን ላይ የተመሰረተ የንግድ፣ የውል እና ሌሎች ጤናማ ስምምነቶች እንዲኖራቸው አገልግሎቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አስረድተዋል።

ስለሆነም አገልግሎቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ የሰነድ ማጭበርበር ወንጀሎችን ለመቀነስ ወጥነት ያለው እና ቀልጣፋ ስርዓት መዘርጋት ይጠበቅበታል ነው ያሉት ።

በመላኩገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.