Fana: At a Speed of Life!

አቶ ውብሸት ደሳለኝ የብሄራዊ ቡድኑ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)አቶ ውብሸት ደሳለኝ የዋሊያዎቹ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና አሰልጣኝ እና ምክትል አልጣኝነት መሾሙ ይታወሳል፡፡

የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ይፋ እንደሚያደርግ ባሳወቀው መሠረትም በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት እየሰሩ የሚገኙት ውብሸት ደሳለኝን መሾሙን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 5 ጨዋታውን ከማላዊ አቻው ጋር ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሞዛምቢክ ስታዲየም እንደሚያደርግ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.