Fana: At a Speed of Life!

ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን በፍጥነት ለመፍታት በአንድነት ልንረባረብ ይገባል – አቶ ጌታቸው ረዳ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትግራይ ክልል ወረዳዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት ህዝባዊ ኮንፈረንስ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ እየመሩት ባለው በዚህ መድረክ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ፣በህዝብ የተወከሉ ተሳታፊች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ÷ መድረኩ በጊዜያዊ አስተዳደር ተልዕኮ ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የክልሉን መልሶ ግንባታ ስራን ለማፋጠን የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚሁ መድረክ፥ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ያለ በመሆኑ በርካታ ጥቄዎችና አስተያቶች ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልፀዋል፡፡

“የሰላም ስምምነቱ ያመጣልንን ፀጋዎች አሟጠን በመጠቀም ያሉንን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በአፋጣኝ ለመፍታት በአንድነት መረባረብ ይገባል” ማለታቸውንም ከጊዜያዊ መስተዳደሩ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.