Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ገበያን የማረጋጋት ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው -አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ገበያን የማረጋጋት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ ገበያን ለማረጋጋት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፥ በክልሉ የቅዳሜ ገበያን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማስቀጠልና በማስፋት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን የማስቻል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ህዝብ ከሚያነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ የኑሮ ውድነት መሆኑን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል በመደበኛው ገበያ የአቅርቦት እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ችግሮች ሲስተዋሉ እንደቆየ አስታውሰው  አሁን ላይ ለሸማቹ እየቀረበ ያለው የምርቶች ዋጋ ከመደበኛው ገበያ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ  እንዳለውም ነው የተናገሩት።

የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እያደረገ የሚገኘውን የደላሎችን ሰንሰለት በመቁረጥና አርሶ አደሩ ምርቶችን ለሸማቹ እንዲያደርስ በማድረግ ገበያን የማረጋጋት ስራው በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.