Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ባንክ የፋይናንስና የግል ሴክተሮች ፕራክቲስ ሃላፊ አልዋሊድ አላባታኒ የተመራ ልዑክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የማሽን ኪራይ ብድር ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ ላይ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ኦፕሬሽን ሃላፊ  ዶይና ፔትሬስኩን ጨምሮ የዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች  ተገኝተዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ ጄት ጨርቃጨርቅና የቆዳ ውጤቶች ስራንና እና አማሄ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተሰኘ ሃይል ቆጣቢ ምድጃ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርትና የስራ ሂደቶችን ተመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወይዘሮ የመንዝወርቅ ግረፌ÷በመንግስትና በፕሮጀክቱ በኩል ለኢንተርፕራይዞቹ ስለተሰጡ ድጋፎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.