Fana: At a Speed of Life!

ሀብታቸው በ24 ስዓታት ውስጥ በ286 ሚሊየን ዶላር ያደገው ቢሊየነር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጆሃን ፒተር ሩፐርት የደቡብ አፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት ሲሆኑ በአፍሪካ ሁለተኛው ከበርቴ መሆናቸው ይነገራል።

የእኒህ ቱጃር ባለሃብት የተጣራ የሀብት መጠን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በ286 ሚሊየን ዶላር እንዳደገ ቢሊየነርስ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ምክንያቱም ከባለሀብቱ ኩባንያዎች አንዱ የሆነውና በዓለም ገበያ ውስጥ በቅንጡ የእጅ ሰዓቶች ፣ ጌጣጌጦችና መሰል የፋሽን ምርቶችን በማቅረብ የሚታወቀው ‘ ሪችመንት ‘ የተባለው ኩባንያ የድርሻ ዋጋው በመመንደጉ ነው ተብሏል፡፡

የኩባንያው የዘንድሮው ገቢ ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር በ19 በመቶ መጨመሩ የተዘገበ ሲሆን ትርፉ ብቻ በ60 በመቶ ጨምሯል ነው የተባለው።

የባለሀብቱ ጆሃን ሩፐርት የተጣራ ሀብት በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በ286 ሚሊየን ዶላር ጨምሮ 13 ነጥብ 7 ቢለየን ዶላር መድረሱም ነው የተነገረው።

ይህም የዓለማችንን 500 ቢሊየነሮች የሀብት እንቅስቃሴ በሚከታተለው ብሉምበርግ ቢሊየነርስ ኢንዴክሰ የተረጋገጠ መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.