Fana: At a Speed of Life!

በመጭው ክረምት 1 ሚሊየን ሄክታር ማሳ በሩዝ ምርት ይሸፈናል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በመጭው ክረምት 1 ሚሊየን ሄክታር ማሳ በሩዝ ምርት እንደሚሸፈን አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ከሁለት አመት በፊት አዲስ የሩዝ ልማት ከ7 ሺህ ሄክታር ባነሰ መሬት መጀመሩን አስታውሰዋል።

የሩዝ ልማቱ ባለፈው አመት ወደ 100 ሺህ ሄክታር ማደጉን ጠቁመው፥ በዚህ አመት 1 ሚሊየን ሄክታር በሩዝ ምርት እንደሚሸፈን አስታውቀዋል።

የሩዝ ምርት ቀጣዩ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ሰብል ይሆናልም ብለዋል፡፡

በቀጣይም የሩዝ ምርትን በማመረት ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.