Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሀፊ ኤሪክ ሚየር ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ወቅት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ፣ ስለ የሽግግር ፍትህ እንዲሁም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለምክትል ረዳት ፀሃፊው ገለፃ አድርገውላቸዋል ።

የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ እና እየታየበት ያለውን እምርታ በሚመለከት ሚኒስትር ዴኤታው ዝርዝር መረጃ የሰጡ ሲሆን፥ ፖሊሲው ሀገሪቱ ከባድ ችግር አጋጥሟት እንኳን የተሻለ ኢኮኖሚ እንዲኖራት ያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከአመት በፊት ከአጎዋ የቀረጥ ነፃ የንግድ ዕድል ተጠቃሚነት እንድትወጣ መደረጉ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደር ምስጋኑ፥ ዳግም ወደ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ግምጃ ቤቱ የድርሻውን እዲወጣ ጠይቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የወደሙ ንብረቶችን መልሶ ለመጠገንና ዜጎችን ለማቋቋም በሚደረገው ሂደት ኢትዮጵያ የአሜሪካን ድጋፍ አጥብቃ እንደምትሻም ሚኒስትር ዴኤታው ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየተሰሩ በሚገኙ ስራዎች ዙሪያም ሚኒስትር ዴኤታው ገለፃ አድርገዋል።

ምክትል ረዳት ፀሀፊው ኤሪክ ሚየር በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል በኢትዮጵያ በኩል እየተሰራ ያለውን በጎ ስራ አድንቀው፥ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

ኤሪክ ሚየር የኢትዮጵያ በኢኮኖሚ መጠናከር ቀጠናውን ጭምር የሚያሳድግ በመሆኑ መንግስታቸውም ሆነ ተቋማቸው ይሄን ከግምት ያስገባ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.