Fana: At a Speed of Life!

“ባክ ቱ ስኩል አፍሪካ” የተሰኘ የትምህርት እና የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ባክ ቱ ስኩል አፍሪካ” የተሰኘ የትምህርት እና የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ተከፈተ፡፡

የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር  ውባየሁ ማሞ(ኢ/ር) በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት÷ቤተ-መጽሐፍቱ ትውልዱ እውቀት የሚያገኝባቸውን የተለያዩ  ሥራዎች እያከናወነ ነው።

የ”ባክ ቱ ስኩል አፍሪካ” አውደ ርዕይ ዋና ዓላማ ወጣቶች የሚሰሯቸውን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እንዲያሳዩ እና ግብዓት እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የተለያዩ ምሁራን በትምህርትና ቴክኖሎጂ አውደ ርዕዩ ላይ ተገኝተው ወጣቶችን እና የፈጠራ ባለቤቶችን የማበረታት እና የማብቃት ስራ እንደሚሰሩም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ የትምህርት ተቋማት፣ በትምህርት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች፣ የመማሪያ ቁሳቁስ አምራቾች እና የተለያዩ የቴክኖሎጂ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.