Fana: At a Speed of Life!

የወጪና ገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠርና በመከላከሉ ረገድ አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል-አቶ ደበሌ ቃበታ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የወጪና ገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠርና በመከላከሉ ረገድ ባለፋት የለውጥ አመታት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል ሲሉ የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተናገሩ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በሠለጠነና ብቁ በሆነ የሰው ሀይል የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ታስቦ  ላለፉት 100 ቀናት  በተለያዩ የጉምሩካዊ ስነ ስርዓቶችና ወታደራዊ ሳይንስ ያሰለጠናቸውን 987 የኬላ ተቆጣጣሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

በመርሃ ግብሩ  የተገኙት  የገንዘብ  ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ  (ዶ/ር) ÷የጉምሩክ ኮሚሽን መንግስት ባለፉት የለውጥ አመታት ሪፎርም ካደረጋቸው ተቋማት መካከል አንድ መሆኑን አንስተው ሪፎርሙ አሁን ላይ በውጤታማነት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም የዛሬው ሰልጣኞችም ሪፎርሙ የበለጠ መሬት እንዲወርድ ብሎም ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ እንዲያድግና ወንጀለኞችን በመከላከል ሂደት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ÷የጉምሩክ ኮሚሽን የወጪና ገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠርና በመከላከሉ ረገድ ባለፋት የለውጥ አመታት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

ሆኖም የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ፣የንግድ ማጭበርበር፣ ሌብነትና ቅን ያልሆነ አገልግሎት አሰጣጥ አሁንም የዘርፋ ፈተናዎች ናቸው ያሉት ኮምሽነር ደበሌ ይህንን ለመከላከል በእውቀትና በክህሎት የዳበረ ባለሙያ ወሳኝ በመሆኑ ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል።

የዛሬ ሰልጣኞችም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የወጣውን ማስታወቂያ መሰረት አድርጎ ፈተና ወሰደው በአጥጋቢ መልኩ ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል ።

በጎህ ንጉሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.