Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች የ7 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የሰባት ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎቹ በአሜሪካ እና ሳዑዲ ዓረቢያ አደራዳሪነት በሳዑዲ ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት ተጠናቋል፡፡

ውይይቱን አስመልክቶ ዋሽንግተን እና ሪያድ ባወጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት÷ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የሰባት ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱም ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ በፊት በተፋላሚ ሃይሎቹ መካከል የተደረሱ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተግባራዊ አለመደረጋቸው ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይ የተደረሰው ስምምነት በትክክል ተግባራዊ እንዲደረግም ሒደቱን የሚቆጣጠር አካል እንደሚዋቀር ተጠቁሟል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ማሰራጨት እና መሠረታዊ አገልግሎቶች ሥራ እንዲጀምሩ ማድረግን እንደሚያካትትም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት እስካሁን በመቶዎች የሚቆየሩ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ ሚሊየኖች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.