Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኮፐንሀገን አዲስ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐንሀገን ዴንማርክ አዲስ በረራ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

በበረራው ማስጀመሪያ መረሐ-ግብር ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ የማኔጅመንት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ፥ አየር መንገዱ በተያያዘው የእድገት መንገድ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን እያሰፋ ይገኛል።

ወደ ዴንማር የተጀመረው አዲስ በረራም ኢትዮጵያን ከዴንማርክ ብሎም ከአፍሪካ ለማስተሳሰር የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በዚህም በሀገራቱ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት፣ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና ቱሪዝምን ለማሳለጥ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የዴንማርክ ካውንስለር ሲቭ ቢያት በበኩላቸው ፥ የበረራው መጀመር በዴንማርክና በኢትዮጵያ መካከል የኢኮኖሚና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብለዋል።

እንዲሁም የሰሜንና አውሮፓ ሀገራትንና የደቡብ እስካንዲኒቪያ ሀገራትን ለማቀራረብ ሰፊ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

በረራው በሳምንት አምስት ጊዜ የሚኖር ሲሆን ፥ ኮፐንሀገን በአውሮፓ 21ኛው መዳረሻ እንደሆነች መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን ፥ በዛሬው እለት ይፋ የሆነው የዴንማርክ የቀጥታ በረራ 134ተኛው አለም ዓቀፍ መዳረሻው መሆኑ ታውቋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.