Fana: At a Speed of Life!

በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ በ76ኛው የዓለም የጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 76ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ጉባዔው “የዓለም ጤና ድርጅት 75 ዓመት ቆይታ፣ ሕይወትን በማዳን፣ ጤና ለሁሉም ለማሳካት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በጉባኤው በኢትዮጵያ አነሳሽነት የተዘጋጀው የተቀናጀ ድንገተኛ፣ ወሳኝ እና ኦፕሬቲቭ ክብካቤ ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን ማሻሻያ ውሳኔ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች እንደሚጸድቁ ይጠበቃል፡፡

የዓለም ጤና ጉባዔ እስከ ፊታችን ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓም ድረስ እንደሚካሄድም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ጉባኤው ከመጀመሩ በፊት በጄኔቭ ከተማ “ዎክ ዘቶክ”የጎዳና ላይ ሩጫ የተካሄደ ሲሆን÷ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች አትሌቶችና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.