Fana: At a Speed of Life!

ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡና ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን ማከናወን ይገባል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡና ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የ100 ቀን የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በሐረሪ ክልል የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በሁሉም የዘርፍ መስሪያ ቤቶች የ100 ቀን ዕቅድ አዘጋጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ግምገማው በየሴክተር መስሪያ ቤቱ የተቀመጡ እቅዶችን በመፈተሽ፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለቀጣይ ስራ ለመዘጋጀት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በ100 ቀናት እቅዱ የክልሉን ሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡና በየስራ ዘርፉ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን ለማከናወን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አቶ ኦርዲን አመላክተዋል።

በግምገማው በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ዑመር በክልሉ የ100 ቀን እቅድ በክትትልና ድጋፍ ቡድኖች የተጠቃለለ የሁለት ወር አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

በሪፖርቱ በክልሉ ገቢን ከማሳደግ፣ ምርትና ምርታማነትን ከማጎልበት፣ የስራ እድልን ከመፍጠር፣ በመንገድ ልማትና የዋጋ ንረትን ማረጋጋትን ጨምሮ ሰላምና ፀጥታ አስመልክቶ የተከናወኑ ስራዎች መቅረባውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.