Fana: At a Speed of Life!

ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማሣደግ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በመቋቋም የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም በየደረጃው ያለው አመራር አቅምና ክህሎቱን በማሣደግ በህዝብ ዘንድ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የመሪነት ሚና እንዲጫወት የሚያስችል መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሣምንት በሚሰጠው ስልጠና የተለያዩ  ይዘት ያላቸው ሠነዶች እንደሚቀርቡ ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.