Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የ3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መድረክ በይፋ ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መድረክ በይፋ ከፍተዋል።

ውድድሩ በስራና ክህሎት ሚኒስትር አዘጋጅነት ‘ክህሎት ለተወዳዳሪነት’ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚቀጥል ነው ተብሏል።

በውድድሩ የፈጠራ ስራዎች ዐውደ ርዕይ፣ ፓናል ውይይትና ሌሎች መርሐ-ግብሮች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ውድድሩ ብቃትና ክህሎት ያላቸው ወጣቶች መብቃታቸውን ለማሳየትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ሁነኛ ሚና ይኖረዋል።

ኢትዮጵያን ለማበልፀግና ሁሉንም ዘርፍ ለማዘመን ፈጠራ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ዘርፎች የግብዓት ችግር ስለሌለ ፈጠራና ክህሎትን ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

የፈጠራ ባለሙያዎች በሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ሳይበገሩ ፈተናዎችን እንደመስፈንጠሪያ ተጠቅመው ውጤት ተኮር ስራዎች ላይ አበክረው እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዕለቱ በቀረቡ የፈጠራ ስራዎችም ትልቅ ተስፋ ሰጭ ፈጠራ ስራዎችን እንደተመለከቱ ገልፀው÷ ሚኒስቴሩ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.