Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት ሜታ ኩባንያን 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ቀጣ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓውያንን መረጃ ለአሜሪካ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ኅብረቱ የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ቅጣት የፌስቡኩ ሜታ ላይ ጣለ፡፡

ኅብረቱ ኩባንያውን በመቅጣት ብቻ ሳይወሰን ከፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ጀምሮ የማንኛውንም የአውሮፓ ሀገራት ተጠቃሚዎችን መረጃ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዶ ማስተላለፍ እንዲያቆም አዟል፡፡

ከዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የአሜሪካ መረጃ መንታፊዎችን በመፍራት እንደሆነ ቪ ኦ ኤ ዘግቧል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ጥብቅ የመረጃ ጥበቃ ሥርዓት ሥራ ላይ ካዋለ አምሥት ዓመታት ወዲህ የአየርላንድ የመረጃ ደኅንነት ጥበቃ ኮሚሽን ኩባንያው ላይ እንዲህ ያለ ቅጣት ሲያሳልፍ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

የሲልከን ቫሊ ቴክኖሎጂ ዋና መሥሪያ ቤት በአየርላንዷ ደብሊን እንደመገኘቱ መጠን በ27ቱ የአውሮፓ ሀገራት ዲጂታል ምኅዳር ውስጥ የሚካሄደውን ማናቸውንም የፌስቡክ ሜታ ግላዊ መረጃዎች የመቆጣጠር ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

የሜታ ዓለም አቀፍ እና የጉዳዮች ፕሬዚዳንት ኒክ ክሌግ እንዲሁም የኩባንያው ዋና የሕግ ኃላፊ ጄኒፈር ኒውስቴድ ÷ የአውሮፓ ኅብረት ያሳለፈው ውሳኔ የተሳሳተ እና ፍትሃዊነት የጎደለው ነው ብለዋል፡፡

ሌሎች በአውሮፓ ኅብረት እና በአሜሪካ መካከል ዲጂታሉን ምኅዳር በመጠቀም መረጃን ለሚያስተላልፉ ሥፍር ቁጥር ለሌላቸው ኩባንያዎችም እንዳይሠሩ የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ ነው ሲሉ መግለጫ ሠጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.