አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በቶጎ ውጫሌ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በቶጎ ውጫሌ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝት መርሐ-ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም በከተማዋ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ፣ የከተማውን የውሃ አቅርቦት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትንና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
አቶ ሙሰጠፌ ከጉብኝታቸው በኋላ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር መምከራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡