Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ እና ዴንቨር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ እና ዴንቨር ከተሞች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ስምምነቱ የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚስችል ነው ብለዋል፡፡
 
ከተማ አስተዳደሩ በዓለም የንግድ ቀን ፕሮግራም ላይም ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ምርቶችን ማስተዋወቁን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች እና ልዑካቸው በዴንቨር ከተማ ለተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶም ለከተማዋ ከንቲባ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.