Fana: At a Speed of Life!

በግብርና፣ በምግብ ማቀነባበሪያና በማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮረ የንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና፣ በምግብ ማቀነባበሪያ፣ በፕላስቲክ ሕትመትና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች ትኩረት ያደረገ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው።

የንግድ ትርዒቱ ከሰኔ 1 እስከ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷ ከ16 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ 130 ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

የፕራና ኢቨንትስ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ በሰጡት መግለጫ÷የንግድ ትርዒቱ በምግብ እሴት ሰንሰለት ላይ የተሰማሩ ዘርፎችን ማስተዋወቅ ያለመ ነው።

በዋናነት የግብርና ምርት፣ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ፣ የምግብ ግብዓት ንጥረ ነገሮችና የመስተንግዶ ሥራዎችን በሚመለከት የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በፓኬጂንግ ዘርፍ የፕላስቲክ ማሸጊያ ቴክኖሎጂና ግብዓቶች የሚቀርቡበት ነውም ብለዋል።

የንግድ ትርዒቱ በዘርፉ ለተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበትና አሠራራቸውን ለማዘመን የልምድ ልውውጥ ይፈጥራል ነው ያሉት።

የፌስ ትሬድ መሴ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፖል ማርዝ በበኩላቸው÷ ይህ የንግድ ትርዒት ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ይበልጥ የሚያበረታታ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የንግድ ትርዒቱም በኢትዮጵያ መካሄዱ ዘርፉ ይበልጥ እንዲያድግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ነው ያሉት።

የንግድ ትርዒቱ በበይነ-መረብም ጭምር የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰው÷ ከተሳታፊ ሀገራትና ኩባንያዎች በተጨማሪ ሌሎች የዘርፉ አካላት ትስስር እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.