Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለው ውይይት አድርጓል፡፡

በአገልግሎቱ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት የልዑካን ቡድን ጋር በነበረው ቆይታ÷በቀጣናዊ፣ ዓለም አቀፋዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት መክሯል።

ከውይይቱ በኋላም ተቋማቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያና የጀርመን የመረጃና የደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትን፣ ሕገወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርን እንዲሁም ሌሎችን ወንጀሎች በጋራ ለመከላከልና የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የስምምነታቸው አካል መሆኑን የአገልገሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.