Fana: At a Speed of Life!

የ“ዋትስአፕ” መተግበሪያ የመልዕክት አርትዖት ሊፈቅድ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዋትስአፕ”ተጠቃሚዎቹ የላኳቸውን መልዕክቶች በ15 ደቂቃዎች ውስጥ ማስተካከል እንዲችሉ ሊፈቅድ መሆኑን አስታወቀ፡፡

“ዋትስአፕ” አገልግሎቱን የሚጀምረው እንደ “ቴሌግራም” እና “ሲግናል” ካሉ ተወዳዳሪዎቹ ጋር ለመፎካከር እንዲያስችለው መሆኑን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

2 ቢሊየን ተጠቃሚዎች ያሉት “ዋትስአፕ” መተግበሪያ፥ ተጠቃሚዎች ከቀጣዮቹ ሳምንታት ጀምሮ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚጀምሩም ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ቀደም ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው የላኳቸውን መልዕክቶች ማረም ወይም ማስተካከል አይችሉም ነበር።

በቀጣዮቹ ሳምንታት የሚጀመረው ይህ አገልግሎት የመተግበሪያውን ተወዳዳሪነት ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ታምኖበታል።

መተግበሪያውን በስፋት በመጠቀም ረገድ በ487 ሚሊየን የተጠቃሚዎች ቁጥር ሕንድ ትመራለች፡፡

“የዋትስአፕ” ተጠቃሚዎች ከላኳቸው በኋላ የሚያስተካክሏቸው መልዕክቶች ላይ “ኤዲትድ” የሚል መለያ ይኖራቸዋልም ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.