Fana: At a Speed of Life!

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ሃርጂት ሳጃን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ላይ እየተሰሩ ያሉና ውጤት የተመዘገበባቸውን የግብርና ልማት ስራዎችን ለካናዳ ዓለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር እና ለልዑካን ቡድናቸው አብራርተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷ በምግብ ዋስትና፣ በአየር ንብረት ለውጥና በብዝሃ ሕይወት፣ በመሬት አያያዝና አጠቃቀም፣ በአፈር ጤንነትና ደህንነት፣ በገበያ ትስስር እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች እንዲሁም የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ሂደት ውስጥ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ በስፋት መክረዋል፡፡

ሃርጂት ሳጃን በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ዘርፉን በማዘመን ሂደት ውስጥ በሚደረጉ ተግባራት ብሎም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን የካናዳ መንግስት ለመደገፍ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.