Fana: At a Speed of Life!

ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ15ኛው ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ድርጅቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም አቢሲኒያ ባንክ 161 ሚሊየን 700 ሺህ ብር እና ብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 5 ሚሊየን እና በኢትዮጵያ የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኩባንያ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.