Fana: At a Speed of Life!

ቤልጄም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ቤልጄም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽንና በአቅም ግንባታ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ( ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከቤልጄም አምባሰደር ስቴፈን ቲጅስ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው÷ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በአይ ሲ ቲ፣ በአቅም ግንባታ፣ በስፔስ ሳይንስና ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ የትብብር ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ ( ዶ/ር) ቤልጄም ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ በትምህርት ዕድል፣ በአቅም ግንባታ እና ሌሎች ላደረገችሁ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

“ይህም ቀጣይ ለምናደርጋቸው የትብብር ስራዎች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እቅዳችንን ለማሳካት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል” ሲሉ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የቤልጄም አምባሳደር ስቴፈን ቲጅስ በበኩላቸው÷ ቤልጄም በዲጂታላይዜሽንና በኢኖቬሽን ከፍተኛ ልምድ ያላት ሀገር እንደሆነች በመግለፅ በዘርፉ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜንና በአቅም ግንባታ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

አምባሳደሩ በቀጣይ የቤልጄም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ወደኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር እንደሚመክሩ ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.