Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንተና እና ትንበያ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 64ኛው የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንተና እና ትንበያ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ፎረሙን የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የአየር ትንበያ ማዕከል ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው ተብሏል።

በፎረሙ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ፣የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክንፈ ኃይለማርያምን ጨምሮ የኢጋድ አባል ሀገራትና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በዓመት ሶስት ጊዜ የሚካሄደው ፎረም በአየር ንብረት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የፓናል ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ፎረሙ የአየር ንብረት ተመራማሪዎችን፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ተጠቃሚዎችን፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ የልማት አጋሮችን፣ ውሳኔ ሰጪዎችን፣ መገናኛ ብዙሃን እና የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት በስሩ አቅፎ የያዘ ነው።

ላለፉት ሁለት ቀናት በባለሙያዎች ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 64ኛው የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንተና እና ትንበያ ፎረም ዛሬ በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ውይይት ይጠናቀቃል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.