Fana: At a Speed of Life!

ታዋቂዋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኟ ቲና ተርነር በ83 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂዋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኟ ቲና ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

በፈረንጆቹ በ1980ዎቹ የፖፕ አቀንቃኝ ለመሆን የበቃችው  እውቋ  የሮክ እና የሮል ኮከብ ቲና ተርነር ከረዥም ህመም በኋላ በ83 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

በቅርብ አመታት የጤና እክል አጋጥሟት የነበረችው ድምፃዊቷ በፈረንጆቹ 2016 የአንጀት ካንሰር እንዳለባት የታወቀ ሲሆን÷ በ2017 ደግሞ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጓም ተገልጿል፡፡

ቲና ተርነር በሮክ እና ሮል የሙዚቃ ስልት የጥቁር ሴቶች ፈርጥ መሆኗን አስመስክራለች።

ከፍተኛ ኃይል  እና ጉልበት የተሞላበት የቀጥታ ትርኢቶቿ  በሙዚቃው  ዓለም  ትልቅ መነሳሳትን እንደፈጠሩ ይገለጻል ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።

“ሪቨር ዲፕ፣ ማውንቴን ሃይ እና ፕራውድ ሜሪ” ታዋቂ ከሆኑት ዘፈኖቿ ተጠቃሾቹ ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.