Fana: At a Speed of Life!

ከ28 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር ከታክስ ስወራ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 10 ወራት ገቢዎች ሚኒስቴር ከ28 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር ከታክስ ስወራ ማዳን መቻሉ አስታወቋል፡፡

የሚኒስቴሩ የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር ብርሃኑ አበበ ባለፉት 10 ወራት 6 ሺህ 716 ታክስ ከፋዮችን ኦዲት ለማድረግ አቅዶ 6 ሺህ 540ዎቹ ላይ ምርመራ በማድረግ የእቅዱን 81 ነጥብ 9 በመቶ ማሳካቱን ተናግረዋል።

በዚህ የኦዲት ግኝት በፍሬ ታክስ፣ በወለድ እና በቅጣት 28 ቢሊየን 684 ሚሊየን 198 ሺህ 675 ነጥብ 44 ብር ገቢ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ይህ የኦዲት ግኝት ያልተገባ ኪሳራን ካስመዘገቡ፣ ተመላሽ ከጠየቁና ተገቢነት የሌላቸው ግብይቶች ከፈጸሙ ድርጅቶች ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኘ ውጤት መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

የምርመራው ግኝት ታክስ ከፋዩ በራሱ ፈቃደኝነት ግብሩን አሳውቆ በወቅቱ ከከፈለው በልዩነት ለገቢ ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተናረዋል፡፡

አክለውም በቀሪዎቹ ሁለት ወራት አቅምን አሟጦ በመጠቀም እቅዱን ማሳካት ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.