Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ የኢፌዴሪ መንግስት በቤጂንግ ያስገነባውን አዲስ የኤምባሲ ህንፃ መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መንግስት በቻይና ርዕሰ መዲና ቤጂንግ ያስገነባው አዲስ ኤምባሲና የመኖሪያ ህንጻ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቻይና የምክር ቤት አባል እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ህንጻውን መርቀው ከፍተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የኤምባሲው አዲስ ገጽታ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የአጋርነት ጠቀሜታ የበለጠ ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ ተጨባጭ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያና የቻይና የቀደመ ግንኙኑት በሁለቱ ሀገራት ማካከል ላለው ጥልቅ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ በባህላዊና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር መሠረት የጣለ ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ ኢትዮጵያ ለቻይና-አፍሪካ ትብብር ስኬት ተምሳሌት ለመሆን ተግታ ትሰራለች ብለዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያና ቻይና የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት በሁለትዮሽ፣ በክልላዊና በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በጋራ እንደሚቆሙ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በበኩላቸው÷አዲሱ የኤምባሲ ህንጻ መገንባቱ የኢትዮጵያ እና የቻይናን ግንኙት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ÷ የኤምባሲው ህንጻ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቻይና ላደረገቸው ያላሰለሰ ትብብር አመስግነዋል፡፡

አጅግ በረረቀቀ መልኩ የተገነቡት የኤምባሲው እና የመኖሪያ ቤቱ ህንጻዎች ለትውልድ የሚተርፍ እንደሆኑ መግለጻቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቻይና የኢፌዴሪ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ባደረጉት ንግግር÷ የኤምባሲው ግንባታ የኢትዮጵያና ቻይና ወዳጅነት ሃውልት ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.