Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ 25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የተላለፉ የዲሲፕሊን ቅጣቶች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በ25ኛ ሳምንት በተካሄዱ ጨዋታዎች የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም በተደረጉ የመርሐ ግብሩ ጨዋታዎች አራቱ በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ ÷ ቀሪ አራቱ ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡

20 ግቦች በ17 ተጫዋቾች የተቆጠሩ ሲሆን÷የግቦቹ አገባብም 17 በጨዋታ ሶስት ደግሞ በፍፁም ቅጣት ምት መሆኑን የሊጉ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሳምንቱ 41 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ፣ አንድ ተጫዋች ደግሞ በሁለተኛ ቢጫ ቀይ ካርድ መመልከቱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ÷ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህ መሰረትም ያሬድ ዳዊት (ወላይታ ድቻ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን ÷ ለፈፀመው ጥፋት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል፡፡

ኤሪክ ካፓይቶ(አርባምንጭ ከተማ)፣ ፍሪምፖንግ ሜንሱ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ረመዳን የሱፍ(ቅዱስ ጊዮርጊስ) እና ዮሴፍ ዮሀንስ(ድሬደዋ ከተማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት 1 ሺህ 500 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።

በሌላ በኩል በድሬደዋ ከተማ እና ለገጣፎ ለገዳዲ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ከአራት በላይ ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ ክለቦቹ የገንዘብ ቅጣት 5 ሺህ እንዲከፍሉ መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የራሳቸውን ቡድን የክለብና የቡድን አመራሮች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን÷ የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት 50 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል።

ወላይታ ድቻ ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን ጨዋታ አመራሮችን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን÷ ከዚህ በፊትም የክለቡ ደጋፊዎቹ አፀያፊ ስደብ በመሳደብ ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው 75 ሺህ ብር እንዲከፍል መወሰኑ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.