Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ በክልሎች እየታየ ያለው የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት እንዲሻሻል አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በክልሎች እየታየ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ ሥርጭት በማሻሻል ለአርሶ አደሩ በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2015 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

ለቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶችም በግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና በሚኒስትር ዴኤታዋ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በውይይቱ ÷ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰሎሞን ላሌ ÷ በዕቅድ አፈፃፀሙ በጥንካሬ እና በቀጣይ ትኩረት ያሻቸዋል የተባሉ ነጥቦችን ባቀረቡት የቃል ግብረ-መልስ አመላክተዋል፡፡

የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ÷ የአፈር ማዳሪያ አቅርቦትና ስርጭት ሊሻሻል እና ወደ ክልሎች የተሰራጨው ማዳበሪያም ለአርሶ አደሩ መድረሱ ላይ ተገቢው ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የማጣራት ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በቀጣይም አማራጭ የሀገር ውስጥ ማዳበሪያን የመጠቀም፣ ለአርሶ አደሩ የተደረገው የማዳበሪያ ድጎማ ተመላሽ የማድረግ፣ የምርጥ ዘር ማዕከላትንና የግብርና ሜካናይዜሽን ስራዎችን የማጠናከር፣ የሌማት ትሩፋትን ማስፋፋትና የምርምር ተቋማትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም አሲዳማ መሬትን በግዥ ብቻ ማከናወን ስለማይቻል ባለኃብቶችንም ማሳተፍ፣ የሕብረት ስራ ማሕበራት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ሚኒስቴሩ ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.