Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዑክ በ7ኛው የአፍሪካ ማንነት መለያ ጉባኤ ላይ ተሳተፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ የኢትዮጵያ ልዑካን የተሳተፉበት 7ኛው የአፍሪካ ማንነት መለያ ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዌሊያም ሩቶ÷ ብሄራዊ የዲጂታል ማንነት መለያ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማድረግ እና በአፍሪካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመዘርጋት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የሕዝብ አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ ለማዳረስ ትክክለኛ የዜጎች መረጃ ያስፈልጋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ የአፍሪካ ብሄራዊ ማንነት አስተዳደር ኤጀንሲዎች በጋራ መስራትና ልምድ መለዋወጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደውን ጉባኤ ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቧን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአፍሪካ መታወቂያ ኮንፈረንስ ላይ ከተለያዩ 40 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፎ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ‘ናሽናል አይዲ ኢትዮጵያ’ ምስጋና አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.