Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ይገባል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ጉድኝት መፍጠርና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

አቶ ደመቀ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ መጽሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቻይና የምርምር ተቋማት ጋር የእውቀት ልውውጥ ማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለው የአማርኛ ቋንቋ ትብብር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛልም ነው ያሉት።

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ጂያ ዌንጂያን በበኩላቸው÷ ቋንቋው በቻይና መሰጠቱ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

በሥነ-ስርዓቱ ሶስት የአማርኛ መመሪያ መጽሐፍት የተመረቁ ሲሆን ÷ ቻይናውያን የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ግጥም ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.