Fana: At a Speed of Life!

ካንሰርን ድል ከመስንሳት  እስከ ክለብ ባለውለታነት – ሰባስቲያን ሃለር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የዌስትሃም ዩናይትድ እና የአያክስ አምስተርዳምስ አይቮሪኮስታዊው አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር የጀርመኑን ክለብ ቦርሺያ ዶርተሙንድ ከተቀላቀለ በኋላ በሀምሌ ወር 2022 የቴስቲኩላር ካንሰር ህመም አጋጥሞት ነበር፡፡

ለህመሙ ከሚሰጠው ሳይንሳዊ ትንታኔ እና በእግርኳስ ተጫዋቾች ላይ ከሚፈጥረው የአካል ብቃት ተፅዕኖ አንፃር ብዙዎቹ የአይቮሪያን አጥቂ የእግር ኳስ ህይወት በ28 አመቱ እንደሚያበቃ ገምተው ነበር፡፡

የሀለርን የእግር ኳስ ጉዞ  በመርሳት ፈጣሪ በህይወት ብቻ እንዲያኖረው የፀለዩም የእግር ኳስ አፍቃሪያን  አልጠፉም፡፡

ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ሃለር የቀዶ ጥገና እና የጨረር (ኬሞቴራፒ) ህክምናውን በማጠናቀቅ በ2023 ጥር ወር  ሀመሙን ታግሎ በማሸነፍ ሙሉ በሙሉ ከካንሰር ነፃ መሆኑን አረጋገጠ፡፡

ከካንሰር ህመሙ ካገገመ በኋላ ወደ ማርቤላ የልምምድ ሜዳ በመመለስ የቦርሺያ ዶርትመንድ የቡድን አጋሮቹን መቀላቀል ችሏል፡፡

ክለቡ በወዳጀነት ጨዋታ ባዝልን በገጠመበት ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ሃለር በ7 ደቂቃዎች ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡

ከህመሙ መልስ ከክለቡ ጋር ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ሃለር በአጠቃላይ ዘጠኝ ጎሎቸን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን፥ ሶስት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

ሃለር ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ በቀረው የጀርመን ቡንደስሊጋ ባለፈው ሳምንት ቦርሺያ ዶርተመንድ ኦግስበርግን ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ክለቡን ወደ መሪነት ማምጣት ችሏል፡፡

የሰባስቲያን ሃለርን ወደ እግር ኳስ መመለስ የፓሪሱ ሌሪየስ ዎርለድ ስፖርት አዋርድ ከክርስቲያን ኤሬክሰን በመቀጠል አስገራሚ አመጣጥ (Greatest Comeback of the Year) ዝርዝር ውስጥ አስቆምጦታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.