Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የጸጥታ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።

በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ከተለያዩ  የክልል፣ ዞንና ወረዳ  የፖሊስ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በውይይቱ÷ፖሊስ  በተሰጠው ኃላፊነት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።

የፖሊስ አባላቱ በክልሉ የህግ የበላይነትን የማስከበርና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ በግንባር ቀደምትነት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ሰሞኑን በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች ተከስቶ የነበረው ችግር በፀጥታ ሀይል የተቀናጀ ጥረት የከሸፈ መሆኑን ጠቅሰው÷አሁን የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.